lamrof
August 6th, 2010, 09:05 AM
ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ተወልደው ያደጉት በቀድሞው አርሲ ክፍለ ሀገር፣ አሰላ አውራጃ፤ ኮፈሌ ወረዳ ልዩ ስሙ ጉቤ በሚባል ቦታ ነው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ጉቤ ት/ቤት፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ኮፈሌ ት/ቤት ነው የተማሩት፡፡
ከዚህ በኋላ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በመግባት በሕግ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ በሥራው ዓለምም በቀድሞው ክልል 14 አስተዳደር የዞን አምስት የአስተዳደር አባል ሆነው ሠርተዋል፡፡ በመቀጠልም የክልል 14 ምክር ቤት አባልና የወቅቱ የማኅበራዊ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሠርተዋል፡፡
በመቀጠልም በአቶ አርከበ ዕቁባይ በሚመራው የአዲስ አበባ ጊዜያዊ አስተዳደር የሥልጣን ዘመን አስተዳደሩ በድጋሚ ሲዋቀር (ከ1995 እስከ 1997) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የማኅበራዊና የሲቪል ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡ ከዚህ በመቀጠል በ1998 ዓ.ም. የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሆነው ሠርተዋል፡፡ በዚህ ቦታ ለሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከሠሩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በድጋሚ በመመለስ የከንቲባ ኩማ ደመቅሳ የሕግ አማካሪና የሊዝና የኅብረተሰብ ጉዳዮች አስተዳደር ዋና የሥራ ሒደት መሪ በመሆን እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ ውድነህ ዘነበ በመሬትና በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙርያ ወ/ሮ ስመኝን አነጋግሯቸዋል፡፡
ሪፖርተር፡- በአቶ አሊ አብዶ የሥልጣን ዘመን በአስተዳደሩ የሥራ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡ በአቶ አርከበ ዕቁባይ የሥልጣን ዘመንም በክፍለ ከተማ ደረጃ የሥራ ኃላፊ ነበሩ፡፡ ከአራት ዓመታት ቆይታ በኋላ በድጋሚ ወደ አስተዳደሩ በመመለስ ትልቅ በሚባል ሥልጣን ላይ ይገኛሉ፡፡ ቀድሞ ከነበሩት የአስተዳደር ወቅቶች አሁን ያለው አስተዳደር በምን ይለያል?
ወ/ሮ ስመኝ፡- መሠረታዊ ልዩነቶች እየመጡ ሔደዋል፡፡ ቀድሞ በነበርኩበት ወቅት የነበረው አሠራር አሁን ካለው አሠራር ጋር የተለያየ ነው፡፡ በዋናነት ለኅብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት ከመስጠት አንጻርና የአጠቃላይ ከተማው መዋቅር ከመለዋወጡ ጋር ተይያዞ፤ የከተማነት ደረጃው እየጨመረ ከመሔዱ ጋር ትናንት ከሚሠራው ሥራ የአሁኑ በዓይነቱም በስፋቱም በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው፡፡ በተለይ ከ1996 ዓ.ም. ወዲህ የከተማው ችግር በዋነኛነት ምንድነው የሚለውን አውቆ ግልጽ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሠራ ነው ያለው፡፡ በጥቃቅንና በአነስተኛ ተቋማት፣ በመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የሥራ አጥነትን ችግርና የመኖሪያ ቤት ችግርን ከመፍታት አንጻር ትልልቅ ሥራዎች በመካሔድ ላይ ናቸው፡፡
ሪፖርተር፡- በአቶ አሊ አብዶ ጊዜ ይህ ሥራ የለም ነበር?
ወ/ሮ ስመኝ፡- አልነበረም፡፡ ይህ የተጀመረው ከመዋቅር ለውጡ ወዲህ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- በቀድሞ አስተዳደር ወቅት የሥራ ቅለት ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የሥራ ክብደቱ ጨምሯል፡፡ በዚህ ሒደት አስቸጋሪ ጉዳዮች አይገጥምዎትም?
ወ/ሮ ስመኝ፡- ተግዳሮቶች አሉት፡፡ በእርግጥ አሁን ያለሁበት ሥራ ከመሬት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በእርግጥ መሬትን በቀጥታ በሊዝ የምንሰጥ ባንሆንም ነገር ግን የሊዝ ጉዳይ የሚያልፈው በሊዝና በኅብረተሰብ ጉዳዮች አስተዳደር በኩል በመሆኑ ከመሬት ጋር የሚገናኙ ቅሬታዎች የሚስተናገዱት እዚህ ረእኔ ዘንድሪ ነው፡፡ ተግዳሮቶቹ አሉ፡፡ ሥራውን ግን ማነጻጸር አይቻልም፡፡ በዚያን ጊዜ ረበአሊ አብዶሪ አይሠራም ማለት አልችልም፡፡ ግን የሥራው ዓይነት፤ የሚሰጠው አገልግሎት እየተለየ ነው የመጣው፡፡ በዚያው መጠን የሥራው መስፋት ብቻ ሳይሆን ሥራው በባሕሪው ለሙስና እየተጋለጠ የመምጣቱ ነገር ከቴክኖሎጂው መስፋት ጋር ተያይዞ ለየት እያለ ነው የመጣው፡፡ ስለዚህ አሁን ያለው ሥራ ለየት ያለ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ሪፖርተር፡- ቀደምት ባሉት የአስተዳደር ወቅቶች የሊዝ ቦርድ ጽ/ቤት ራሱን ችሎ የተዋቀረ ነበር፡፡ አሁን ባለው አስተዳደር ደግሞ ከማኅበራዊ ጉዳዮች ጋር ነው የተዋቀረው፡፡ ሊዝና ማኅበራዊ ጉዳይን ምን አገናኛቸው?
ወ/ሮ ስመኝ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ መሬት በምን አግባብ እንደሚሰጥ የሚደነግግ ደንብ አውጥቷል፡፡ ይህንን ደንብ የሚያስፈጽሙ ዝርዝር ጉዳዮችን የያዙ መመሪያዎችም ወጥተዋል፡፡ ከእነዚህ መመሪያዎች አንዱ መመሪያ ቁጥር አንድ በመባል የሚታወቀው የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመስጠት የወጣው የአፈጻጸም መመሪያ አንዱ ነው፡፡ ይህ መመርያ አሥራ ሦስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ መሬት በምን አግባብ እንደሚሰጥ፣ ቅሬታ በምን አግባብ እንደሚቀርብ፣ ግንባታ በምን መልኩ እንደሚካሔድና እንደሚጠናቀቅ ያስቀምጣል፡፡ በዚህ መመሪያ መሠረት መሬት በአምስት መንገዶች ይሰጣል፡፡ እነሱም በጨረታ፣ በድርድር፣ በዕጣ፣ በሽልማትና በምደባ ናቸው፡፡ ከነዚህ መካከል ትልቁ መሬት የሚሰጥበት መንገድ ጨረታ ሲሆን፣ ይህ ሥራ በክፍለ ከተሞች የሚካሔድ ነው፡፡ እኛን በቀጥታ የሚመለከትን የድርድር ጉዳይ ነው፡፡ ድርድር የሚካሔድባቸው ለከተማው የተሻለ ልማት ያመጣሉ ተብሎ የታመነባቸው ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡
ለምሳሌ ኢንዱስትሪዎች፣ ከአራት ኮከብ በላይ የሆኑ የሆቴል ግንባታዎች፣ ሙሉ በሙሉ በውጭ ኢንቨስተር የሚካሔዱ ፕሮጀክቶች፣ ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ግንባታዎች፣ ለሆስፒታሎችና ለጤና ምርምር ተቋማት ግንባታ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል፡፡ በኛ የሥራ ሒደት ውስጥ ሁለት ኬዝ ቲሞች አሉ፡፡ የሊዝ ጉዳይና የኅብረተሰብ ጉዳይ ኬዝ ቲሞች ናቸው፡፡ ሁለቱም ኬዝ ቲሞች በዋነኝነት የሚሠሩት የኅብረተሰቡን ቅሬታ ተቀብሎ ማስተናገድ ነው፡፡ በሊዝ ጉዳይም በኅብረተሰብ ጉዳይም በኩል የሚመጡ አቤቱታዎች አሉ፡፡ የበፊቱ ሊዝ ቦርድና የአሁኑ መዋቅር የተለያዩ ናቸው፡፡ ሥልጣናቸውም የተለያዩ ናቸው፡፡ አሁን በተካሔደው የመሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ ጥናት የሊዝና የኅብረተሰብ ጉዳይ የሥራ ሒደት ተብሎ ሁለቱን ባማከለ መልኩ ነው የተዋቀረው፡፡ የማኅበረሰብ ጉዳይ ነው ብለን የምንይዘው ለምሳሌ የሰላማዊ ሠልፍ ፈቃድና የመሳሰሉት ሁሉ እኛ ሥር ናቸው፡፡
ሪፖርተር፡- ቀደም ሲል የሰላማዊ ሠልፍ ዝግጅት ማሳወቂያ ክፍል በፍትሕ ቢሮ ሥር ነበር?
ወ/ሮ ስመኝ፡- አሁን እኛ ዘንድ ነው፡፡ የኅብረተሰብ ጉዳይ ስለሆነ እኛ ዘንድ መጥቷል፡፡
ሪፖርተር፡- የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወቅሷችኋል፡፡ ምክንያቱም ሕጉ የሚለው ማሳወቅ ነው፤ እነሱ ሲያሳውቋችሁ በተለያዩ ምክንያቶች ስብሰባው ወይም ሰላማዊ ሠልፉ እንዳይካሔድ ታደርጋላችሁ?
ወ/ሮ ስመኝ፡- ይህ የሚያሳየው ካለመረዳት የሚመጣ ተቃውሞን ነው፡፡ እኛ እንዲያውም እጅግ የተሻለ ሥራ እየሠራን ያለንበት ዘርፍ ነው፡፡ ትልቁ ችግር ምንድነው ዝግጅቱን ሊያካሒድ ያቀደው አካል ዝግጅቱን የሚያካሒድበትን ቀን ወስኖ ይመጣል፡፡ በዚያ ቀን ደግሞ ሌላ አካል ቦታውን ይዞት ይሆናል፡፡ ስለዚህ በዚህ ቀን ሌላ አካል ይዞታል፣ ቀን ቀይሩ ብለን ስንገልጽ እኔ ያልኩት ካልሆነ እያሉ የሚቆጡ አሉ፡፡
ሪፖርተር፡- መስቀል አደባባይ ላይ ስብሰባ ወይም ሠልፍ ለማካሔድ ፓርቲዎች ቀን ቆርጠው መጥተው ያሳውቋችኋል፡፡ እናንተ ደግሞ መካሔድ እንደማይችል ምናልባትም አደባባዩ በዚያ ቀን ለሌላ ጉዳይ የተየዘ መሆኑን ትገልጻላችሁ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጊዜው ደርሶ አደባባዩ ሲታይ ምንም የሚካሔድበት ፕሮግራም የለም፡፡
ወ/ሮ ስመኝ፡- መስቀል አደባባይ ላይ ከምርጫው ጋር ተያይዞ የትኛውም ፓርቲ ሊጠቀም እንደማይገባ ስምምነት ነበር፡፡ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) እንኳ የተመሠረተበትን በዓል መስቀል አደባባይ ላይ ለማክበር ነበር ጥያቄ ያቀረበው፡፡ በምርጫው ወቅት የትኛውም ፓርቲ አይጠቀምበትም ስለተባለ ለኦሕዴድም ጭምር አንፈቅድም ብለናል፡፡
ሪፖርተር፡- ምክንያታችሁ ምንድን ነው?
ወ/ሮ ስመኝ፡- ዋናው ችግር እንደዚህ ዓይነት ቦታ ላይ ሰላማዊ ሠልፍ ሲካሔድ ስጋት አለ፡፡ መንግሥት የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተበታተነና ለጥበቃ አመቺ ባልሆነ ሁኔታ ላይ በብዛት ሕዝብ ይወጣል፡፡ ይህንን ሕዝብ መቆጣጠር ባይቻልና የሰው ሕይወት ቢጠፋ መንግሥት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ አደባባይ ላይ ሳይሆን ስታዲዮም እንዲያደርጉት፣ ሚሊኒየም አዳራሽ እንዲያደርጉት፣ ጃንሜዳ እንዲያደርጉት መክረናል፡፡ ስለዚህ ኢሕአዴግንም ጭምር ከልክለናል፡፡
ሪፖርተር፡- ምርጫው በተካሔደ ማግስት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በተገኙበት ኢሕአዴግ ትልቅ ሰላማዊ ሠልፍ መስቀል አደባባይ ላይ አድርጐ አልነበር እንዴ?
ወ/ሮ ስመኝ፡- ገደቡ የተቀመጠው እስከ ምርጫው ወቅት ነው፡፡ ምርጫው ከተካሔደ በኋላ ነው ኢሕአዴግ ዝግጅቱን ያካሔደው፡፡
ሪፖርተር፡- የእርስዎ ጽ/ቤት ተዋቅሮ እርስዎም ከተሾሙ ጊዜ ጀምሮ ከሌሎች ጽ/ቤቶች በተለየ የእርስዎ ጽ/ቤት በባለጉዳዮች ይጣበባል፡፡ ምክንያቱ ምንድን ነው?
ወ/ሮ ስመኝ፡- በነገራችን ላይ ዓመታዊ ግምገማችንን በቅርቡ አካሒደን ነበር፡፡ በዚህ ግምገማ ባለጉዳይ እየጨመረ ነው ወይስ እየቀነሰ ነው የሚለውን ገምግመናል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ባለጉዳይ እየቀነሰ መሆኑን ነው የተረዳነወ፡፡ ባለጉዳይ ይበዛል? አዎ ትክክል ነው፡፡ የሚበዛው ለምንድን ነው? ጉዳዮቹ በራሳቸው የሆነ ችግር ስላላቸው ነው፡፡ ብዙዎቹ ሕገወጥ ይዞታ ይዘው ሕጋዊ እንድናደርግላቸው የመፈለግ አዝማሚያ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ሕገወጡን ሕጋዊ ማድረግ አንችልም፡፡ ሕጋዊ የሆነውን ብቻ ነው የምናስተናግደው፡፡ አንዳንዱ ካርታ ሳይኖረው ካርታ እኛ ዘንድ እንደሚሰጥ አድርጐ የሚያስብ አለ፡፡ አንዳንዱ የያዘው ካርታ ሕገወጥ ሆኖ ሲመክንበት ያለ አግባባ ካርታዬ መከነብኝ ብሎ ወደኛ የሚመጣ አለ፡፡ እያንዳንዱ ባለጉዳይ ወደኛ ይመጣል ምክንያቱም የኛ ጽ/ቤት ምንም ገደብ የለውም፡፡ የትኛውም ባለጉዳይ የትኛውንም ጉዳይ ይዞ ወደእኛ ስለሚመጣ ባለጉዳይ በዝቶ ሊታይ ይችላል፡፡
በአጠቃላይ ግን ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ የባለጉዳይ ቁጥር በጣም ቀንሷል፡፡ በተለይም በሊዝ ጉዳይ በጣም ቀንሷል፡፡ የሊዝ ጉዳይ ቅሬታዎች ይበዙ የነበሩት በ1989 ዓ.ም. እና በ1990 ዓ.ም. ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ውሳኔ የተሰጣቸውና ቦታውን ግን ያልተረከቡ ሰዎች ነበሩ፡፡ የከተማው አስተዳደር ከዚህ ቀደም በሊዝ ቦርድ የተወሰነን ውሳኔ አከብራለሁ በማለቱ ይህንን ችግር ለመፍታት ከኛ ጽ/ቤት፣ ከመሬት አስተዳደርና የግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን፣ ከከተማ ማደስና የመሬት ባንክ ጽ/ቤት የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ፣ ጉዳዮቹ አንድ በአንድ እየታዩ ለሊዝ ቦርድ መቅረብ ያለባቸው እየቀረቡ ቦርዱ ዘንድ ሳይደርስም ውሳኔ እየተሰጠ ተፈተዋል፡፡ ጥቂት ብቻ ናቸው የቀሩን፡፡
ሪፖርተር፡- እኔ ያነጋገርኳቸው የእርስዎ ባለጉዳዮች ግን ቤቴ ሕገወጥ ተብሎ ፈረሰ፤ በአቶ አርከበ ጊዜ ቦታ ተወስኖልኝ እስካሁን መረከብ አልቻልኩም የሚሉ ይገኙበታል፡፡
ወ/ሮ ስመኝ፡- በግብረ ኃይል ፈረሰብኝ የሚሉ ቅሬታዎች በሕገወጥ ይዞታ እስከተያዙ ድረስ ዛሬም ነገም ሊፈርሱባቸው እንደሚችል ማናችንም የምንቀበለው ይመስለኛል፡፡
ሪፖርተር፡- ሕጋዊ የሆነውስ ባለይዞታ?
ወ/ሮ ስመኝ፡- ቦታ የያዘ ሁሉ ራሱን እንደ ሕገወጥ ያለማየት ችግር አለበት፡፡ በቃ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ይገባኛል የማለትና እንደመብት የማየት አመለካከት አለ፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ሁሉም ባለይዞታ ሕጋዊ ማረጋገጫ ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህንን እስካልያዙ ሕጋዊ ነው ልንለው አንችልም፡፡ ልንረዳውም አንችልም፡፡ ዕርምጃው ትክክል ነው የምንለው፡፡ ከዚህ ባለፈው ያለአግባብ ከሆነ ግን አጣርተን ምላሽ የምንሰጣቸው ደግሞ በርካቶች አሉ፡፡ ያለአግባብ ዕርምጃ የተወሰደበት አካል ካለ ማለት ነው፡፡
ሪፖርተር፡- ከኪራይ ቤቶች ጋር በተያያዘ፣ ለአንዱ የተሰጠውን ቦታ በድጋሚ ለሌላ ወገን የተሰጠባቸው፣ ፍርድ ቤት ላይ ባለ ጉዳይና በመሳሰሉት ላይ ግብረ ኃይል አቋቁማችሁ ችግራቸውን የምትፈቱበት አሠራር አላችሁ?
ወ/ሮ ስመኝ፡- እንደዚህ ዓይነቱን በግብረ ኃይል የምንመለከተው ጉዳይ አይደለም፡፡ ነባር ይዞታ ሆኖ፣ ቦርዱ ወስኖላቸው ለረጅም ጊዜ መረከብ ያልቻሉትን ግብረ ኃይል ተቋቁሞ የሚወሰንላቸው አሉ፤ ቅድም ከገለጽኩልህ ጋር ተያይዞ፡፡ ከኪራይ ቤቶች ጋር የሚገናኙ ጉዳዮችን ከመሬት አስተዳደርና የግንባታ ፈቃድ ጋር ሆነን በተቀመጠው መመርያ መስፈርት ነው የምንፈታው፡፡ ለየት ያሉ ጉዳዮች ሲመጡ ከኃላፊዎች ጋር አንድ ላይ በመሆን መፍትሔ እንሰጣለን፡፡
ሪፖርተር፡- ለእነዚህ ይህ ነው የሚባል የአሠራር መስፈርት አላችሁ? ይህንን የጠየቅኩዎች "ደብል ስታንዳርድ" ወይም ሁለት ዓይነት የአሠራር መስፈርት አላችሁ ተብላችሁ ስለምትወቀሱ ነው፡፡
ወ/ሮ ስመኝ፡- ምንም ዓይነት "ደብል ስታንዳርድ" የለንም፡፡ አሠራራችን ግልጽ ነው፡፡ የወጣው መመርያ ደግሞ እያንዳንዱን ጉዳይ በግልጽ ሊፈታ የሚችል መመርያ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ከነባር ይዞታዎች ጋር ተያይዞ ለከተማው አስተዳደር ራስ ምታት የነበረው ነባር ይዞታ ያላቸው ነዋሪዎች ካርታ ስለሌላቸው ይጉላሉ ነበር፡፡ ይህንን ለመፍታት የሚያስችል የፕሮጀክት ጽ/ቤት ተቋቁሟል፡፡ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ ይህ በመጀመሩ ወደእኛ የሚመጡ ባለጉዳዮች እዛው እየተፈታላቸው በመሆኑ እኛ ዘንድ አይመጡም፡፡
ሪፖርተር፡- ዕርምጃ አወሳሰድን በተመለከተ አንድ ዓይነት ዕርምጃ አትወስዱም፣ አንዱ ላይ ፈጣን ናችሀ፣ ሌላው ላይ ትዘገያላችሁ፡፡ እናም ለዚህ ነው "ደብል ስታንዳርድ" አላችሁ እያስባለ የሚያስወቅሳችሁ፡፡ ለምሳሌ በሪል ስቴቶች ላይ ዕርምጃችሁ የዘገየ ነው፡፡
ወ/ሮ ስመኝ፡- በነገራችን ላይ ግለሰቦች ለኢንቨስትመንት ቦታ ወስደው ለረጅም ዓመታት ግንባታ ባለማካሔዳቸው የወሰድነው ዕርምጃ አለ፡፡ ቦታውንም ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ የተደረገበት ሁኔታ አለ፡፡ በተረፈ በሪል ስቴት ላይ ያነሳኸው ትክክል ነው፡፡ ሪል ስቴቶችን በተመለከተ ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ አስተዳደሩ በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ መመርያዎችን አውጥቷል፡፡ የተሰጡ በርካታ ቦታዎች አሉ፡፡ ቦታዎቹ ሕገወጥ ተግባሮች ተከናውነውባቸዋል፤ ለሦስተኛ አካል ተላልፈዋል፡፡ ስለዚህ ይህንን ውስብስብ ችግር በአንድ ቀን መወሰን አይቻልም፡፡ በተሰጡት ቦታዎች ላይ የብዙ አካላት እጆች አሉበት፡፡ በቦርዱ ውሳኔ ተወስኖ የተሰጠ ቦታ ነው፡፡ ቦታው ደግሞ ምን ዓይነት ደረጃ ላይ እንዳለ መጠናት አለበት፡፡ ስለዚህ ጥናት ተካሔደ፣ ከአልሚዎቹ ጋር ውይይት ተደረገ፣ ከእዚህ በኋላ ያለው ሁኔታ በቦርዱ እየታየ ነው፡፡ የአፈጻጸም መመርያ ሊወጣለት ስለሚገባ እንደየትኛውም ቦታ ውሳኔ የሚሰጥበት አይደለም፡፡ ግማሹ ግንባታ ጀምሯል፤ አንዳንዱ ከተሰጠው ቦታ ላይ በጥቂቱ ላይ ብቻ ገንብቷል፡፡ ከውሉ ውጭ ሰርቪስ ቤት የገነባ አለ፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን ለማኅበራት የተሰጡ ቦታዎች ላይም ተመሳሳይ ጥናት እየተካሔደ ነው፡፡ መመርያው ሲጸድቅ ዕርምጃው ይቀጥላል፡፡
ሪፖርተር፡- ከባለአደራው አስተዳደር ሊዝ ቦርድ ወደ እርስዎ ጽ/ቤት የተዘዋወሩ የመሬት ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ አልሚዎች ገንዘባቸውን በዝግ ሒሳብ አስቀምጠው ነበር ቦታው እስኪሰጣቸው ሲጠብቁ የነበረው፡፡ አብዛኛዎቹ በእናንተ ውሳኔ ደስተኞች አይደሉም፡፡
ወ/ሮ ስመኝ፡- አንድ ነገር ግልጽ መሆን አለበት፡፡ በፊት የነበረው አሠራር ለምሳሌ ነባር ይዞታ ያለው ሰው፣ የመንግሥትም ይሁን የግል ቦታ ያለው ሰው ቅድሚያ የማልማት መብት ነበረው፡፡ ቅድሚያ ቦታው ላይ ላለው አካል መብት ተሰጥቶት ማልማት ይችላል የሚል አሠራር ነበር፡፡ ይህ አሠራር ብዙዎቹ ሰዎች ቅድሚያ የማልማት መብት አለን በሚል ለዘመናት ቦታውን ቢይዙም፣ አስተዳደሩ በሚፈልገው ፍጥነት ወደ ልማት መግባት አልቻሉም፡፡ ይህ ለከተማውም ሆነ ለአገርም አዋጭ ሆኖ ስላልተገኘ አስተዳደሩ ይህንን አሠራር ቀይሮታል፡፡ ሙሉ በሙሉ ለነባር ባለይዞታዎች ቅድሚያ የሚለው አሠራር እንዲቀር ተደርጓል፡፡ ቅድሚያ ለነባር ባለይዞታዎች የሚባለው በአዲሱ አሠራር ቦታ የለውም፡፡ ስለዚህ እንደ ፕሮጀክቱ ጠቀሜታና የፕሮጀክቱ ባለቤት እንደሚያቀርበው የፕሮጀክት ሁኔታ ላይ ተንተርሰን ነው የምንሠራው፡፡ ተደራጅተው በዝግ ሒሳብ ገንዘብ አስቀምጠው ቅድሚያ የማልማት መብታችን ይጠበቅ ያሉትን ብዙዎቹ ላይ አስተዳደሩ ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡
ሪፖርተር፡- ውሳኔው ምንድን ነው?
ወ/ሮ ስመኝ፡- ገንዘባቸው ከነወለዱ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡
ሪፖርተር፡- በዚያን ጊዜ ባለሦስት ኮከብ ሆቴል መገንባት በባለአደራው አስተዳደር ትኩረት የሚሰጠው ነበር፡፡ ይህንን ለመገንባት በዝግ ሒሳብ ገንዘብ አስቀምጠው ሲደራደሩ የቆዩ ነበሩ፡፡ ከሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ይህ ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ አስተዳደሩ ትኩረት ያደረገው ባለአራት ኮከብ ሆቴል ላይ ስለሆነ ጥያቄው ውድቅ መሆን ነበረበት? የተቃጠለው ጊዜ ታሳቢ አይደረግም? ይህንን የምጠይቀው የቀድሞው አስተዳደር ይህንን አሠራር ስለሚከተል የግሉ ዘርፍ በዚህ መሠረት ጊዜውንና ጉልበቱን አጥፍቷል እና ነው፡፡
ወ/ሮ ስመኝ፡- ታሳቢ ማድረግ ከተገባ ከተማ ውስጥ ወሳኝ የተባሉ ቦታዎች በአላስፈላጊ ልማቶች ሊያዙ ይችላሉ፡፡ በእኔ እምነት ታሳቢ ያለመደረጉ ትክክል ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ምክንያቱም ከተማው ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ ነው መሔድ ያለበት፡፡
ሪፖርተር፡- አሁን ለቦርዱ የምታቀርቧቸው ምን ያህል የድርድር ቦታ ጥያቄያዎች አሉ?
ወ/ሮ ስመኝ፡- በእጃችን ምንም የለም፡፡ የመሬት አስተዳደርና የግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን የመሬት ጥያቄ ይቀበላል፡፡ በደንቡ መሠረት የቀረበ መሆኑን መርምሮ ለውሳኔ ለኛ ጽ/ቤት ያቀርባል፤ እኛ ለቦርዱ እናቀርባለን፡፡ ከዚያም ቦርዱ ይወስናል፡፡ በነገራችን ላይ ቦርዱ መሰብሰብ ያለበት በወር አንድ ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን እንደጉዳዩ አስፈላጊነት ከወር ባነሰ ጊዜ እንደሚገናኝ ተደንግጓል፡፡ ስለዚህ ጉዳዮች በርከት ብለው ከቀረቡ ቦርዱ በሳምንትም በሁለት ሳምንትም ተሰብስቦ ይወስናል፡፡ በእኛ እጅ እየተጉላላ የተቀመጠ ጉዳይ የለም፡፡
ሪፖርተር፡- እርስዎ አዲስ አበባ ላይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወዳድረው አሸንፈዋል፡፡ አሁን ባሉበት ጽ/ቤት ከተሾሙ አንድ ዓመት አይሞላዎትም፡፡ እዚህ ይቆያሉ ወይስ ሌላ መ/ቤት ይሔዳሉ?
ወ/ሮ ስመኝ፡- አዎ፣ ተወዳድሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርጫለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ የት እንደምመደብ አላውቅም፡፡ ድርጅቴ ነው የሚመድበኝ፡፡ በእርግጥ የፓርላማ አባል ነው የምሆነው፡፡ ከፓርላማ አባልነት ውጭ ለተጨማሪ ሥራ የሚመድበኝ ድርጅቴ ነው፡፡ ለፌዴራል ልሁን እዚሁ ልቀጥል አሁን ላይ ሆኜ የማውቀው ነገር የለም፡፡
ሪፖርተር፡- አሁን ባሉበት ቦታ አንድ ዓመት ሊሞላዎት ነው፡፡ አሳክቼዋለሁ ብለው የሚያስቡት ምንድን ነው?
ወ/ሮ ስመኝ፡- እኔ ያን ያህል አሳካሁ የምለው ነገር የለም፡፡ ዋናው ነገር ቅሬታ ይዞ የሚመጣው ባለጉዳይ ቢሮዬ መጥቶ ሳይጉላላና ሳይመላለስ ተገቢውን መረጃ ይዞ እንዲሔድ የማድረግ ሥራ ነው የምንሠራው፡፡ ለዚህም ነው ባለጉዳይ የቀነሰው፡፡ የማይሆን ጥያቄ ይዞ ሚመጣ ከሆነ በግልጽ እንነግረዋለን፡፡ በእኔ እምነት የተለየ ተሳክቶልናል የምንለው ጉዳይ የለም፡፡ ባለጉዳዮች ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ግን የተሻለ እየሠራን ነው የሚል ዕምነት አለኝ፡፡