View Full Version : የውጭ ዜጋ ካገቡ ኢትዮጵያዊያት ትዳር ጀርባ


lamrof
July 20th, 2011, 12:48 AM
http://www.ethiopianreporter.com/component/content/article/305-woman/2681-2011-07-16-10-35-53.html....

ከኖርዌጂያኑ ባለቤቷ ጋር ለአንድ ዓመት በጓደኝነት ቆይተው ትዳር ከመሠረቱ ሦስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ‹‹ዕቃ ለኔ ገዝተን በታክሲ ወደ ቤት በመመለስ ላይ ነበርን፡፡ ሒሳብ አውጥቼ ስከፍል በአለባበሱና በገጽታው ደህና የሚመስልና ከጐኔ ተቀምጦ የነበረ ጐልማሳ ‘በኋላ ሒሳብሽ ላይ የሚደመር ነው?' ሲል ተናገረኝ›› በማለት ከውጭ አገር ዜጋው (ፈረንጅ) ባለቤቷ ጋር ሰዎች ሲመለከቷት ከሰነዘሯቸው አስተያየቶች አንዱን ነገረችን፡፡ እንደዚህ ያሉ ያልተገቡ አስተያየቶች ብቻም ሳይሆኑ ዘለፋዎችም ያጋጥሟታል፡፡....

....የሰዎች ጣልቃ ገብነት የታየው፣ ዘለፋና ያልተገቡ አስተያየቶች የተሰነዘሩት በገነት የትዳር ሕይወት ብቻ አይደለም፡፡ የውጭ ዜጋ ያገቡ እንዲሁም ከውጭ ዜጐች ጋር የፍቅር ግንኙነት የመሠረቱ ብዙዎች ተመሳሳይ አስቸጋሪ ሁኔታ ዕለት በዕለት ያጋጥማቸዋል፡፡....

....ሌላዋ ስሟ እንዲገለጽ ያልፈለገች የሃያ ስምንት ዓመት ወጣት ደግሞ፣ ምንም እንኳ ጋብቻ ባይፈጽሙም፣ ከአንድ እንግሊዛዊ አንድ ልጅ ወልዳለች፡፡ እሷም የገነት ዓይነት አስተያየቶችን በተለያዩ ጊዜያት አስተናግዳለች፡፡ እንደምትለው፣ ብዙ ኢትዮጵያውያት የውጭ ዜጐችን ሲያገቡ በብዛት ስለማይታይ፣ የእሷንና የገነትን ዓይነት የፍቅር ግንኙነት ወይም ትዳር ማኅበረሰቡ በቀላሉ ሊቀበለው አይችልም፡፡ በርካታ ጥያቄዎችን ያነሣል፤ የተለያዩ መላምቶችን ይሰነዝራል፤ ከተሳሳቱ ድምዳሜዎች ላይም ይደርሳል፤ ዘለፋና ነቀፋም አይጠፉም፡፡....


....ገነትም ተመሳሳይ ነገር አጋጥሟት ያውቃል፡፡ እሷን እንደጥሩ አርአያ የምትመለከታት የቅርብ ጓደኛዋ ባለቤቷ አንድ ቀን ጥሏት ወደ መጣበት መመለሱ እንደማይቀር በግልጽ ነግራታለች፡፡ ሠርቶ ራስን በመቻል እንደምታምን፤ ሁለተኛ ዲግሪዋን ለመሥራት በምን ዓይነት ሁኔታዎች እንዳለፈች የሚያውቅ ሌላ የቅርብ ጓደኛዋም የዛሬው ኑሮዋ በጥረቷ የተገኘ ሳይሆን የውጭ ዜጋ የማግባቷ ውጤት እንደሆነ እንደሚያስብ በአንድ አጋጣሚ ገልጾላታል፡፡....

lamrof
July 20th, 2011, 12:49 AM
Sorry, can't stand seeing Ethio women with "ሻሾ"