View Full Version : Boat Design & Assembly | Lake Tana Transport Enterprise


yosef
December 14th, 2011, 08:52 PM
Constructed at Lake Tana in Bahir Dar

Boat Name: Nigat
Size: 22 meters long, 5.50 meters wide
Capacity: 350 HP, 120 people
Duration of Construction: 179 days bottom deck, 151 top deck
Cost: ~Birr 7 million
Video: (at about 5:40 min in) http://www.allcomtv.com/etv-vod?etvod=2011121418


Construction

http://img59.imageshack.us/img59/3930/32682850.png

http://img859.imageshack.us/img859/7004/53451029.png

http://img4.imageshack.us/img4/5580/54721818.png

http://img202.imageshack.us/img202/8395/94901053.png

http://img705.imageshack.us/img705/4544/90445317.png

http://img834.imageshack.us/img834/1282/24212506.png



Finished Product

http://img6.imageshack.us/img6/496/17180826.png

http://img851.imageshack.us/img851/6366/41795333.png

http://img807.imageshack.us/img807/5663/85292911.png

http://img859.imageshack.us/img859/404/82654707.png

Yoniii
December 14th, 2011, 09:02 PM
Well...it's a start. :)

abesha
December 14th, 2011, 09:38 PM
Is it made from scratch? Including engine, etc?

It's a good start for sure.

abnet
December 15th, 2011, 03:38 AM
More detail from last Sunday Reporter amharic news.


እስከ 80 ሚሊዮን ብር የሚያስወጣ ጀልባ በስምንት ሚሊዮን ብር ተሠራ

Sunday, 11 December 2011 00:00
By WUDINEH

ጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ድርጅት ከ70 እስከ 80 ሚሊዮን ብር ሊያስወጣው ይችል የነበረውን ጀልባ፣ በስምንት ሚሊዮን ብር ወጪ በአገር ውስጥ መሥራቱን አስታወቀ፡፡

ለጣና ሐይቅ ከጣናነሽ ጀልባ ቀጥሎ ሁለተኛውና ንጋት የሚል መጠርያ የተሰጠው ግዙፍ ጀልባ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሚገኙበት ታህሳስ 8 ቀን 2004 ዓ.ም. ይመረቃል ተብሎ ዕቅድ ተይዟል፡፡

ከጣናነሽ ሌላ በሐይቁ ላይ የሚንቀሳቀሱ የድርጅቱ ጀልባዎች በአንድ ጊዜ ከ40 ሰው በላይ መጫን አይችሉም፡፡ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፈንታ በየነ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአካባቢው የሚገኙ ጥንታዊ የቱሪስት መስህቦችን ለመጐብኘት በብዛት የሚመጡ ቱሪስቶችን ማስተናገድ አስቸጋሪ ነበር፡፡ የአዲሲ ጀልባ መገንባት ይህንን ችግር በሚገባ ይቀርፈዋል ሲሉ አቶ ፈንታ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

አዲሱን ጀልባ ለመገንባት 15 ባለሙያዎች መሳተፋቸውን፣ እነዚህ ባለሙያዎች በዋናነት ከጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ድርጅት የተውጣጡ ሲሆን፣ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲና የትራንስፖርት ባለሥልጣን ባለሙያዎች በማማከር ሥራ መሳተፋቸው ታውቋል፡፡

በ1977 ዓ.ም. ሰሜን ኮሪያ ለኢትዮጵያ ወታደራዊ መንግሥት ጀልባ ማምረት የሚያስችሉ መሣሪያዎች መግዛት እንዲያስችለው ስድስት ሚሊዮን ብር ከወለድ ነፃ ብድር መስጠቷ ይታወሳል፡፡ የጀልባው በቀይ ባህር ሐሌብ ደሴት ግንባታ ኢሕአዴግ አገሪቱን እስከተቆጣጠረበት 1983 ዓ.ም. ድረስ ቢቀጥልም፣ ኤርትራ ነፃ በመውጣቷ ፕሮጀክቱ ባክኖ እንደቀረ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በዚያን ጊዜ ሐሌብ ደሴት ላይ ሲካሄድ በቆየው የጀልባ ግንባታ ሥራ ላይ ከተሳተፉ ባለሙያዎች መካከል ሦስቱ በጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ይሠሩ ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ሥራ የለቀቁ ሲሆን፣ አንደኛው በአዲሷ ጀልባ ግንባታ ተሳታፊ ናቸው፡፡ አዲሲቱ ጀልባ የሚያስፈልጓት ሞተርና ተያያዥ ዕቃዎች የመጡት ከጃፓን ሲሆን፣ 5.4 ሚሊዮን ብር ወጥቷል፡፡ ብረት እንጨትና ለጀልባዋ የማስዋቢያ ዕቃዎች ከአገር ውስጥ ገበያዎች ተሟልተዋል፡፡

አቶ ፈንታ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የጀልባዋ ሙሉ ዕቃዎች ከውጭ ተገዝተው ቢመጡ ኖሮ የጀልባዋ ወጪ ከ70 እስከ 80 ሚሊዮን ብር ይፈጅ ነበር፡፡ ጣና ሐይቅ ትራንስፖርት 11 ጀልባዎች ነበሩት፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ግዙፏ ጣናነሽ ነች፡፡ ከ11 ጀልባዎች ሦስቱ በብልሽት ሲቆሙ የተቀሩት በሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡

ጣና ከባህር ዳር እስከ ጎንደር አዋሳኝ አካባቢዎች ሰፊ ቦታ ይዞ የሚገኝ ሐይቅ ነው፡፡ ርዝመቱ 84 ኪሎ ሜትር፣ ስፋቱ ደግሞ 66 ኪሎ ሜትር ነው፡፡ በዚህ አካባቢ በርካታ ሕዝብ የሚገኝ በመሆኑ ድርጅቱ የትራንስፖርትና የዕቃ ማጓጓዝ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ የኅብረተሰቡን የመጓጓዢያ ፍላጎት ለማሟላት አራት ጀልባዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ይህንንም ለማሟላት የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን አቶ ፈንታ ገልጸዋል፡፡