SkyscraperCity Forum banner

በጣም የመሰጠኝ ገለጻ እና ለኣቅራቢው የላኩት መልዕክት።

178 Views 1 Reply 1 Participant Last post by  begtera
http://ethsat.com/video/esat-yetimihirt-bilichita-by-dr-tadesse-opportunism-part-5-april-30-2014/


ሰላም አቶ ታደሰ።


በቅድሚያ «አቶ» በሚለው የክብር ኢትዮጵያዊ ስም ቅጥያ የተራሁዎት በኔ አመለካከት «ዶ/ር» የሚለው የማዕረግ ጥሪ እንደ ሌላው የነጭ ወይንም አውሮፓዊ ሥርዓት በኢትዮጵያውያን ምሑራን ዘንድ ያለቅጥና ያለአግባብ ጥቅም ላይ ሲውል በማየቴ ከዘመናት በፊት ይህንን ጥሪ፣ ሙያዊ አግባብ በሚኖርበት ዓውድ ውስጥ ካልሆነ በስተቀር በፍፁም ላለመጠቀም ከራሴ ጋር ቃል በመጋባቴ ነው። «አቶ» የሚለው ኢትዮጵያዊ የክብር አጠራርም ሥብዕናዊ ክብደትና ትርጉም ያለው በመሆኑ በዚህ የክብር አጠራር ጠርቼዎታለሁ።


እ'ልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል፤ እንዲሉ ያለወትሮዬ ከኢሳት ድረ-መካን ስዋዥቅ የርስዎን ዝግጅት አዳመጥኩ። በእውነት «የልብ አውቃ» የሚለውን ብሂል አስታወሰኝ። የጠቀሷቸው ጸኃፊ በብዙ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ያለን ጉዳይ ርቱ'ዕ በሆነ ቋንቋ አስቀምጠውታል። እርስዎም ይህንን ግዜያዊና ነገራዊ አግባብ ያለውን ገለፃ ተገንዝበው በዝግጅትዎ ላይ እንደ ርዕስ አቅርበውታል።


አንድን ህዝብ ሃገር የሚያደርገው ልዩ የሆነው የባሕሉ ይዘት፣ የአስተዳደር አወቃቀሩ፣ አምልኮቱ፣ ማሕበራዊ ደንቦቹ፣ የተጻፉትም ሆነ ያልተጻፉት ሥርዓቶቹ፣ ዓለማዊ ርዕዮቱ እና የሰዉ ሰብዓዊ ሰበዝና የመሳሰሉት ናቸው። አንድ ሰው ወይንም ህዝብ የራሱን ውርስና ቅርስ ትቶ የጎረቤቱን ካየ፣ ሃገራዊ ፅናቱ ተናግቷል፣ ለውጪ ጥቃት ተጋልጧል ማለት ነው። ኃያላን ሃገራት ኃያል የሆኑበት ምክንያት እንደ ህዝብ ለሃገራዊ መለዮ ያላቸው አመለካከት ለዑል ስለሆነ ነው። ሮማውያን ስለሮማዊነት የነበራቸው አመለካከት ሌላ ሃገራት ስለራሳቸው ከነበራቸው እይታ እጅግ የላቀና የፀና ነበር። በኋላ ግን ይህ ርዕዮት በውስጣዊ ግፍ እየተሸረሸረና ለውጪ ውስወሳ እየተጋለጠ ሲሂድ፣ ሮም ውስጧ በስብሶ ለውድቀት በቃች።


በእኔ እይታ በሚኒሊክ ግዜ የጀመረው አውሮፓዊ የሆኑ ዘዴዎችን ወደ ኢትዮጵያ የማስገባት ጥረት አንድ መሠረታዊ ህጸጽ የያዘ ነበር። ይህም ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ በመቅረብ (ወይንም በራሳቸው አውሮፓውያን መሰሪ ደባ) አዘምኑኝ አሰራራችሁን አልምዱኝ ብላ ስትቀርብ፡ ተያይዞ የመጣው አመለካከት ኢትዮጵያ ኋላ ቀር ወይንም ጭራሹን ሥልጡን አለመሆኗ ነበር። ይህ ታላቅ አመለካከታዊ እንከን በጊዜው በነበሩትም በኋላም በተከተሉት አሰራሮች ላይ እጅግ ጎጂ መዘዝ ይዞ ዘልቋል። በእኔ አመለካከት ዘመናዊንትና ሥልጣኔ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። እሱን ለግዜው ልተወውና ሰለጀመርኩት የአመለካከት ህጸጽ ልግለጽ።


ኢትዮጵያዊ ወጣቶች ወደ ውጪ ለትምህርት በሚላኩበት ግዜ የአሰራር ዘዴዎችን ብቻ ሳይሆን አውሮፓዊነትንም ተምረው የመለሱ ነበር። ኢትዮጵያ በሚመለሱበትም ግዜ በህዙም በራሳቸውም አመለካከት ኢትዮጵያዊነትን አውልቀው ነጭነትን ወይንም አውሮፓዊነትን ተከናንበው የመጡ ልዩ ዜጋዎች ሆነው በመቆጠር አርዓያ በመሆነ በመኳንቱና በነገሥታቱ ዘንድ ልዩ ክብር ይሰጣቸው ነበር። አውሮፓዊ አለባበስ፣ አነጋገር፣ አመጋገብ በጣም ሲከፋ ደግሞ አውሮጳዊ ርዕዮታትን መከተል ሥልጣኔ ሆነ። መማር ማለት ከኢትዮጵያዊነት መላቀቅ ሆነ። የተማረው ወደራሱ ውርስ ቅርስ ሳይሆን ወድ ውጪ ማተኮር ጀመረ። ገጠር ኢትዮጵያ ከአዲሳባ የተለየች እንደሆነች ተደርጎ አዲሳባ ብቻ በመስፈር ከተማይቱን አዎሮፓዊ «ኦአሲስ» የማድረጉ ሂደት ቀጠለ። በጉራማይሌ ቋንቋ ወይንም ከነአካቴው በፈረሳይኛ ወይንም እንግሊዝኛ መናገር ሙያ ሆነ።


እርሶ እንደጠቀሱት የዚህ ህጸጽ ርዝራዥ በ 60 ዎቹም አሰርት ዓመታት በመታየት፣ የግራ ፍልስፍናን ተክኖ እንዳለ ከውጭ ገልብጦ አምጥቶ ኢትዮጵያዊ ውስጥ መዶል ሙያ ሆነ። ይህንን አመለካከትም ጎድን ያለው ማንም አልነበረም። ኢትዮጵያና ህዝቦቿ የዚህ ጥፋት ገፈት ተቋዳሽ ሆኑ። ወጣቶቿ ተሰደዱ፣ በሰው ሃገር የ'እንጀራ ዜጎቹ ሆኑ። አሁን ያለው አስተዳደራዊ ምስቅልቅልም እውን ሆነ።በጣም የሚያሳዝነው ጉዳይ ይህንን አመለካከት አሁን ነፍስ ያወቀነው ለልጆችቻን እያወረስነው መሆኑ ነው። ተስፋ የሚሰጠኝ ግን እንዲህ እርሶ እዳቀረቡት ያለ ዝግጅትና አስተምህሮት ሳይ ነው።


በዝግጅቱ በጣም ነው የረካሁበት። አዘውታሪ አድማጭ እሆናለሁ።


ይበርቱ።
በግተራ ነኝ
ከካሊፎርኒያ
See less See more
  • Like
Reactions: 2
1 - 2 of 2 Posts
ESAT Yetimihirt Bilichita <[email protected]>
to:Begtera <[email protected]>
date: Mon, May 5, 2014 at 6:15 PM
subject:Re: ESAT Yetimihirt Bilichita by Dr Tadesse Opportunism Part 5 April 30 2014
mailed-by: ethsat.com

በግ ተራ፤

በጣም እጅግ በጣም አመሰግናለሁ።
የቀደሙትንም ፕሮግራሞች ሰምተው አስተያየት ቢሰጡኝ በጣም ደስ ይለኛል።
የእርስዎን ዓይነት የሞራል ድጋፍ ካገኘሁ ፕሮግራሙን ጥሩ ማስተማሪያ ማድረግ ይቻላል።

ከማክበር ሰላምታ ጋር።
ታደሰ
See less See more
1 - 2 of 2 Posts
This is an older thread, you may not receive a response, and could be reviving an old thread. Please consider creating a new thread.
Top