የአዲስ አበባ ከተማን የሕንፃዎች ከፍታ ደንብ ለማሻሻል የተጠናው ጥናት ይፋ መሆኑን አዲስ ልሳን ዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ አርክቴክቸር፣ ሕንፃ ግንባታና ከተማ ልማት ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ጋር በገባው ውል መሠረት የአዲስ አበባ ከተማን የሕንፃዎች ከፍታ ለማሻሻል የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱ ተገልጿል፡፡ ጥናቱ ይፋ በሆነበት ወቅት እንደተለገጸው፣ በከተማዋ የሚገነቡ ሕንፃዎች የአገሪቱን ገፅታ የሚያስተዋውቁና የከተማዋን መሬትና መሠረተ ልማት በሚገባ መጠቀም ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሕንፃዎቹ ከተማዋን የሚያሳድጉ፣ የከተማዋን ባህልና ታሪክ ጠብቀው የሚያቆዩ፣ እንዲሁም ለሥራም ሆነ ለኑሮ የሚመቹ መሆን እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡