Joined
·
1,596 Posts
This news says they will open it the coming Sunday.They charge 50 Eth birr($2.50 USDollar) for small cars, medium size cars will pay 60 Eth birr($3.00 USDollar) and big cars 70 Eth birr ($3.50 USDollar) for the whole 76 Kilometers use (upto Adama) .I hope that it's finally opened for general traffic when I visit on November. But you never know![]()
http://www.ethiopianreporter.com/index.php/news/item/7220-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%8B%B3%E1%88%9B-%E1%8B%A8%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%8B%AB-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%88%E1%8B%B5-%E1%8A%A8%E1%88%98%E1%8C%AA%E1%8B%8D-%E1%8A%A5%E1%88%91%E1%8B%B5-%E1%8C%80%E1%88%9D%E1%88%AE-%E1%88%A5%E1%88%AB-%E1%8B%AD%E1%8C%80%E1%88%9D%E1%88%AB%E1%88%8Dየአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ ከመጪው እሑድ ጀምሮ ሥራ ይጀምራል
10 September 2014 ተጻፈ በ ዳዊት ታዬ
- ለመንገዱ ግንባታ የወጣውን ወጪ እስከ 20 ዓመት ለመመለስ ታቅዷል
ክፍያ የሚጠየቅበት የመጀመሪያ መንገድ የሚሆነው የአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድ ከመጪው እሑድ መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ አገልግሎት ይጀምራል፡፡ በፍጥነት መንገዱ ለመጠቀም እንደተሽከርካሪዎቹ ዓይነት በአንድ ኪሎ ሜትር 0.66፣ 0.72 እና 0.92 ሣንቲም እንደሚሆን የሚታወቅ ቢሆንም፣ የአከፋፈል ሥርዓቱ ግን የተለየ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
የፍጥነት መንገዱን ለማስተዳደር የተቋቋመው የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሕይወት ሞሲሳ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የክፍያ መንገዱ ከእሑድ ጀምሮ ክፍት ስለሚሆን አሽከርካሪዎች በዚህ መንገድ መጠቀም ይችላሉ፡፡
76 ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው የፍጥነት መንገዱ ክፍል ማሽከርከር የሚቻለው በሰዓት ከ100 እስከ 120 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ፍጥነት ነው፡፡ ለፍጥነት መንገዱ አገልግሎት የተተመነው ዋጋ በሦስት ደረጃ የተከፋፈለ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ክፍል የተካተቱት አነስተኛ የሚባሉ ተሽከርካሪዎች ለአንድ ኪሎ ሜትር 0.66 ሣንቲም ይከፍላሉ፡፡ ሙሉውን ወይም 76 ኪሎ ሜትር መንገዱን ከተጠቀሙ የሚከፍሉት 50 ብር ይሆናል፡፡ በሁለተኛ ክፍል የተቀመጡት መካከለኛ የሚባሉ ተሽከርካሪዎች በአንድ ኪሎ ሜትር 0.72 ሣንቲም ይከፍላሉ፡፡ በሦስተኛ ደረጃ የሚቀመጡት ትላልቅ ተሽከርካሪዎች በመባል የተለዩት ደግሞ በአንድ ኪሎ ሜትር 0.92 ሣንቲም እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡ በዚህ ዋጋ መሠረት መካከለኛ የሚባሉት ተሽከርካሪዎች ሙሉ 76 ኪሎ ሜትሩን ከተጠቀሙ 60 ብር፣ ከፍተኛ ወይም ትላልቆቹ ተሽከርካሪዎች ተብለው የተለዩት ደግሞ 70 ብር እንደሚከፍሉ ታውቋል፡፡
እንደ ወ/ሮ ሕይወት ገለጻ፣ የክፍያ ሥርዓቱ እንደተሽከርካሪው ዓይነት በአንድ ኪሎ ሜትር የተተመነው ዋጋ በተጓዘበት ኪሎ ሜትር ተባዝቶ የሚሰላ ቢሆንም፣ ሽርፍራፊ ገንዘብ እንዳይኖር ክፍያውን አምስት ብርን መሠረት ያደረገ የተለየ አከፋፈል ሥርዓት ይኖረዋል፡፡
ይህም አሠራር ለምሳሌ አንድ ተሽከርካሪ የ22 ብር ከሠላሳ ሣንቲም የሚያስከፍል መንገድ ከተጓዘ እንዲከፍል የሚደረገው ሃያ ብር ነው፡፡ 13 ብር ከሃምሳ ዋጋ የሚጠየቅበት አገልግሎት ካገኘ ደግሞ የሚከፍለው 15 ብር ይሆናል ተብሏል፡፡ በዚሁ ሥሌት መሠረት በየአምስት ብር ልዩነት ይከፈላል፡፡
ይህ አሠራር ለቅልጥፍና የተደረገ በመሆኑ፣ የክፍያ ሥርዓቱ ኮምፒዩተራይዝድ ሆኖ የሚሠራና ተገልጋዩ መክፈል የሚገባውን ዋጋ በግልጽ አይቶ እንዲከፍል የሚያስችል ነው፡፡ ኮምፒዩተራይዝድ ሥርዓቱ ሽርፍራፊ ሳንቲሞችና ገንዘቦችን አስቀርቶ በየአምስት ብር ልዩነት ያለውን ዋጋ ያሳያል ተብሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ወጪ የሆነው 11 ቢሊዮን ብር ኢንተርፕራይዙ ቢዘገይ እስከ 20 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ለመመለስ ማቀዱ ተገልጿል፡፡ ይህም ኢንተርፕራይዙ ለጥገናና ለመሳሰሉት ጉዳዮች የሚያወጣውን ወጪ ቀንሶ የሚከፍል በመሆኑ ነው፡፡ ለመንገዱ ግንባታ የወጣው ወጪ ከቻይና ኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር የተሸፈነ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በኢንተርፕራይዙ ዕቅድ በመጀመሪያው የሥራ ዘመን በ2007 ዓ.ም. ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት እንደሚችል፣ ይህ ዕቅድ ግን በየዓመቱ ይቀየራል ተብሏል፡፡
ኢንተርፕራይዙ አገልግሎቱን ከመጀመሩ ጋር ተያይዞ ለተገልጋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች የሚሠራ መሆኑን፣ ከዚህ መንገድ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የወጡ ድንጋጌዎችም ተግባራዊ የሚደረጉ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ከኢንተርፕራይዙ በተገኘው መረጃ መሠረት ለክፍያ መንገዱ ከወጡ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች መካከል፣ ክፍያ ሳይከፍል በመንገዱ ሲጓዝ የተያዘ አሽከርካሪ ከመንገዱ መነሻ እስከ መድረሻ ድረስ ያለውን ታሪፍ በእጥፍ እንዲከፍል ይደረጋል የሚለው አንዱ ነው፡፡ ከተፈቀደ ፍጥነት መጠን በላይና በታች ማሽከርከርም ያስቀጣል፡፡
የተጭበረበረ የአገልግሎት ክፍያ ትኬት መያዝ ደግሞ ከወንጀል ተጠያቂነት በተጨማሪ፣ የመንገድ አገልግሎቱ ክፍያ አምስት እጥፍ ያስቀጣል፡፡ በክፍያ መንገዱ ውስጥ የተበላሸ መኪናን በ30 ደቂቃ አለማንሳትም 100 ብር ቅጣት ያስከትላል፡፡ ከተፈቀደለት የጭነት ልክ በላይ ጭኖ በመንገዱ የተጠቀመ ቅጣት የሚጣልበት ሲሆን፣ የክፍያ መንገዱ አጥር ውስጥ የገባ እግረኛም የ50 ብር መቀጮ እንደሚጠብቀው ስለክፍያ መንገድ የወጣው አዋጅ ይደነግጋል፡፡
አዲሱ ኢንተርፕራይዝ ከተቋቋመባቸው ዋና ዋና ዓላማዎች መካከል የክፍያ መንገዶችን ማስተዳደርና መጠገን እንዲሁም በክፍያ መንገድ ውስጥ የተገነቡ የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ማስተዳደርን ያካትታል፡፡
ኢንተርፕራይዙ እንደ አንድ አትራፊ የመንግሥት የልማት ድርጅት ነው የተቋቋመው፡፡ የተቋቋመበት ካፒታል 200 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ከዚህ በኋላም የሚገነቡ የፍጥነት መንገዶች በዚህ ኢንተርፕራይዝ ሥር ይተዳደራሉ፡፡
በፍጥነት መንገዱ ውስጥ መንገዱን ጨምሮም የተለያዩ ግንባታዎች ቢጎዱ ጥገና የማድረግና የመንከባከብ ኃላፊነቱ የኢንተርፕራይዙ እንደሆነም ታውቋል