SkyscraperCity Forum banner

Cars & More

1233 Views 8 Replies 7 Participants Last post by  AM2
Hello guys! Selamta lehulachihu yidress...

I am new here, you seem to have a pretty nice forum.

So, please do allow me to ask you some questions around cars and exporting them from Europe to Ethiopia. What do I have to know before sending a used car to Addis?

I just want to sell my 12-year-old car in Addis. Is it a good idea at all to send a used car to Ethiopia?

I look forward to your opinion.

Thanks
1 - 1 of 9 Posts
^^
ለምሳሌ፡- የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 70,000፣ የሲሊንደር አቅሙ 1280 የሆነ አዲስ ቶዮታ ኮሮላ አውቶሞቢል ቢገባ፤ ቀረጥና ታክሱን ለመወሰን የሚከተሉት አምስት የስሌት ደረጃዎች ይሰላሉ፡፡ የመጀመሪያው የጉምሩክ ቀረጥ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ መጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 70,000 X 35/100 = 24,500 ይሆናል፡፡

በቀጣይ የሚሰላው ኤክሳይዝ ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይዝ ታክስ መጠን (70,000 + 24,500) x 30% = 28,350 ይሆናል፡፡

በሶስተኛ ደረጃ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስ በመደመር በተጨማሪ እሴት ታክስ ሬት ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ እሴት ታክስ ብር (70,000 + 24,500 + 28,350) X 15% = 18,427.5 ይሆናል፡፡

በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350+ 18,427.5) X 10% = 14,127.75 ብር ይሆናል፡፡

በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 70000 x 3/100 = 2100.00 ብር ይሆናል፡፡

በመጨረሻው የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክሶች ይደመራሉ፣ በዚህ መሰረት መንግስት ከአውቶሞቢሉ የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት ድምር 24,500 + 28,350+ 18,427.5 + 14,127.75 + 21,000 = 87505.25 ብር ይሆናል:
What *******s!! The taxes are actually cumulative?! This is ripping people off in the first degree. You're paying taxes on taxes ... unbelievable
  • Like
Reactions: 3
1 - 1 of 9 Posts
This is an older thread, you may not receive a response, and could be reviving an old thread. Please consider creating a new thread.
Top