
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የተጐዱ የከተማውን ክፍሎች ለማልማት በያዘው እቅድ መሰረት ከልደታ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ጀምሮ እስከ መናኸሪያ ያለውን አካባቢ አፍርሶ የማልማት ሥራ ጀመረ፡፡ ተፈናቃዮቹ የተለያዩ አማራጮች ተሰጥቷቸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መኩሪያ ኃይሌ አርብ እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት መስተዳደሩ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ተከታታይ ውይይት ካደረገ በኋላ አካባቢውን አፍርሶ የማልማት ሥራው እንዲጀመር መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ አቶ መኩሪያ እንዳሉት በግንባታው ምክንያት ከአካባቢው ለሚፈናቀሉት 1300 ነዋሪዎች ይዞታቸውን መሠረት በማድረግ የተለያዩ አማራጮች ተሰጥቷቸዋል፡፡ በቀበሌ ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች አቅም ካላቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ገዝተው እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ አቅም የሌላቸው ደግሞ ሌላ የቀበሌ ቤት ተፈልጐ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ከኪራይ ቤቶች እና ከቀበሌ ጋር ኮንትራት ተፈራርመው ንግድ እየነገዱ የነበሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ራሳቸውን አደራጅተው የኮንዶሚኒየም ቤት ዓይነት ህንፃ የሚገነቡበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን የገለጹት አቶ መኩሪያ፣ የራሳቸው መኖሪያ ቤት ያላቸው ነዋሪዎች ደግሞ ከፈለጉ በያዙት ይዞታ መጠን መሬት የሚያገኙበት ሁኔታ መመቻቸቱን፣ አካባቢው ሲለማ መመለስ እንፈልጋለን ካሉ ደግሞ ምርጫቸው የተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከልደታ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ጀምሮ እስከ መናኸሪያ ያለው የመጀመሪያ የመልሶ ማልማት ሥራ በ26 ሄክታር መሬት የሚካሄድ ሲሆን የትምህርት ቤት እና የጤና ጥበቃን ጨምሮ ሁሉም ዓይነት የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲከናወኑ ይደረጋል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ከመስቀል አደባባይ እስከ ካራማራ ባለው አካባቢ የሚኖሩ 420 ነዋሪዎች እንዲነሱ ተደርጐ ቀደም ሲል በሊዝ ቦታ ገዝተው ማልማት ላልቻሉ ባለሃብቶች የሚስተናገዱበት ሁኔታ እንደሚመቻች አቶ መኩሪያ ገልጸዋል፡፡ በተለምዶ አጠራር ባሻ ወልዴ ችሎት ተብሎ የሚጠራው አካባቢ በያዝነው ዓመት ሰፊ የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት የሚካሄድበት አንዱ አካባቢ ነው፡፡
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በካርታ ሥራ ኤጀንሲ በስተጀርባ ያለው አካባቢ ነዋሪዎችም አካባቢያቸው መልሶ እንዲለማ ፍላጎት ያላቸው መሆኑን የጠቆሙት አቶ መኩሪያ ይሄው የመልሶ ማልማት ሥራ በዘንድሮው ዓመት እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡ በዚህ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች የቀበሌ ቤትም ሆነ የራሳቸውን ቤት ማደስ ያልቻሉበት ሁኔታ መፈጠሩን በመግለጽ ግፊቱ ከራሳቸው ከነዋሪዎቹ መምጣቱን ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡
አብዛኛዎቹ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ከከተማ ውጭ በመሰራታቸው አነስተኛውና መካከለኛው የኅብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ አለመሆኑን በመጥቀስ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት አቶ መኩሪያ፣ አዲስ አበባ በ540 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ የምትገኝ ከተማ እንደመሆኗ መጠን በየትኛውም አቅጣጫ ቢኬድ ሩቅ ነው ሊባል የሚችል ቦታ አለመኖሩን ጠቁመው በአሁኑ ሰዓት ያለው የትራንስፖርት እጥረት ከተፈታ ችግሩ መፍትሔ እንደሚያገኝ ገልጸዋል፡፡
መሬት ተረክበው ማልማት ያልጀመሩ ባለሃብቶችን በተመለከተም ከ1996 ጀምሮ የግንባታ መጀመሪያ ጊዜ ገደብ ያለፈባቸው ቦታዎች ለመስተዳድሩ ገቢ እየተደረጉ መሆኑን፣ የግንባታ ፈቃድ አልፎባቸው አሳማኝ ምክንያት ያቀረቡ፣ በመስተዳድሩ የመዋቅር ድክመት ምክንያት ላቀረቡት የግንባታ ፈቃድ ቶሎ ምላሽ ያላገኙ ካሉ ደግሞ ጉዳዩን ለሊዝ ቦርድ ካቀረቡ ፈቃድ የሚያገኙበት ሁኔት መኖሩን ተናግረዋል፡፡
ከመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ያለው መንገድ እንደገና እንደሚሰራ እየታወቀ በመንገድ መሀል ያለው ደሴት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት በብረትና በሰንሰለት ማጠር ለምን አስፈለገ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት አቶ መኩሪያ ከመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ያለው መንገድ እስከሚሠራ ድረስ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን የምታካሄደውን የአዲስ አበባ ከተማን ውበት ለመጠበቅ ሲባል ደሴቱ በቋሚ ብረትና በሰንሰለት እንዲታጠር መደረጉን፣ የመንገዱ ግንባታ ሲጀመርም ሰንሰለቱና ብረቱ ተነቅሎ ሌላ ቦታ ላይ የሚተከልበት ሁኔታ እንደሚኖር አስረድተዋል፡፡ አቶ መኩሪያ እንዳሉት ከመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ያለው መንገድ የታጠረበትን ብረት ለመንቀል ከሚወጣው የሰው ጉልበት ውጪ የሚያመጣው ኪሳራ የለም፡፡
http://www.ethiopianreporter.com/in...view=article&id=996:2010-01-24-09-25-43&catid=98:2009-11-13-13-41-10&Itemid=617
If you used to live in the Lideta area growing up, then in a few years you will not be able to recogize the area any more.
Side note: I am not sure if they are doing it, but we need to have space for kids to play, not just buildings. Most of our memories growing is not about a building its about the games we played in the neighborhood.
My prediction is that in the near future residents in Addis will have to travel outside the city on the weekends to find open space and play sports and have fun.